የአፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ በላሊበላ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የክልል አፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ ከነገ ጀምሮ በላሊበላ ከተማ ይካሄዳል፡፡
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ እና ምክትል አፈ-ጉባዔ ሽታዬ ምናለ ላሊበላ ገብተዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አደም ፋራህ እና ምክትል አፈ-ጉባዔ ዕፀገነት መንግስቱ እንዲሁም የክልል አፈ-ጉባዔዎች ላሊበላ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደረጎላቸው፡፡
የላሊበላ ከተማ ከንቲባ አቶ ይልማ መርቅ ለአፈ- ጉባዔዎቹ ልኡካን አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አፈ-ጉባዔዎቹ ከአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ ከሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የላሊበላ ውቅር አብያተ-ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል፡፡
በዚሁ በላሊበላ ከተማ የፌዴራል እና የክልል አፈ-ጉባዔዎች የምክክር መድረክ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!