Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ህዝብ የሀገር ቀጣይነትን ለማረጋገጥ በታላቅ ሀገራዊ ፍቅር የከፈለው መስዋዕትነት ሲታወስ ይኖራል- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል በአፋር ክልል በአሸባሪዉ ህወሃት ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች የ10 ሚሊየን ብር የአይነትና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክልሉ ያደረገው ድጋፍ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚሆን የህክምና ቁሳቁስ እና በጥሬ ገንዘብ የ3 ሚሊየን ብር ነው ።

በአፋር ክልል ተገኝተው ተጎጂዎችን የጎበኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ÷ የአፋር ህዝብ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በፍቅርና በአንድነት የሚኖር እና በሀገር የማይደራደር ህዝብ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያን ለማፅናት ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈሉን አንስተው በዚህም ሁሌም በኢትዮጵያውያን ዘንድ በታሪክ ሲታወስ ይኖራል ብለዋል።

አሸባሪው ህውሃት ህዝብን በጭካኔ ጨፍጭፏል፤ መሰረተ ልማትን ማውደሙን ጠቁመው በዚህም የሽብር ቡድኑ ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት አስመስክሯል ሲሉ ተናግረዋል።

የሀረሪ ክልል በአፋር ክልል የወደሙ ሶስት የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋምና ስራ ለማስጀመር እየሰራ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው ÷አሸባሪው ህውሃት በአፋር ክልል 10 ቢሊየን ብር የሚሆን የመሰረተ ልማት ማድረሱን ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ በሀገርና በዜጎች ላይ ካደረሰው የጭካኔ ተግባር ባሻገር የኢትዮጵያውያንን አንድነት እንዲጠናከር እድል መፍጠሩን ማመላከታቸውን ከሃረሪ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የተመራ ልዑክ በአፋር ክልል በሽብርተኛው ህወሓት ቡድን ተጎጂ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጎብኘትና መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዛሬ ሰመራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.