Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ስድስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤ ሹመቶችን በማጽደቅና የሥራ አቅጣጫን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን ጉባኤ ዛሬ ሲያጠናቀቅ ሹመቶችን ያጸደቀው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ያቀረቧቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ሃላፊዎችን ነው።
በዚህ መሰረትም፣
1ኛ አቶ ሙሳ አብደላ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
2ኛ አቶ አብዱሠላም አህመድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እና
3ኛ አቶ አህመድ መሀመድ የክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።
የምክር ቤቱ ጉባኤ የቀረቡለትን የእነዚህን ሃላፊዎች ሹመት በመቀበል በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአፋር ክልል ያለምንም የጸጥታ ችግር ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በየደረጃዉ የሚገኙ የምክር ቤቶች አባላት ህብረተሰቡን በማንቃት የማስተባባርሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡም አሳስቧል።
ለህዝቦች አብሮነት ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ እንዲፈቱ ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከል በመንግስትና ሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ሰው በሚበዛባቸው የአገልግሎት መስጫ ድርጅቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ልምድ እንዲጎለብት የምክር ቤቱ አባላት የመሪነት ሚናቸው እንዲወጡ በክልሉ ጤና ቢሮ የቀረበውን ምክረ-ሃሳብ ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ጉባኤው መጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.