Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት ስለ ኦሚክሮን ስርጭት መረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ስለስርጭት ሁኔታ ለመግለፅ አስቸጋሪ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሀገራት ስለ ኦሚክሮን የኮረና ቫይረስ ስርጭት የተሟላ መረጃ ባለመስጠታቸው ስለበሽታው ስርጭት ሁኔታ መናገር አስቸጋሪ እንዳደረገበት የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር ማዕከል (ሲ ዲ ሲ) ገለፀ።

በአፍሪካ የሲዲሲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ጆን ንከንጋሶንግ እንዳሉት፥ ደቡብ አፍርካ በአህጉሪቱ ብቸኛዋ ስለበሽታው ስርጭት ሁኔታ የተሟላ መረጃ የምታቀርብ ሀገር ናት።

በሀገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት እና በቫይረሱ ተይዘው ወደ ሆስፒታል የመግባት ሁኔታም በሳምንት እስከ 9 በመቶ መቀነሱን ነው ያመለከቱት።

27 በመቶ የሚሆነውን ህዝቧን የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ በሲዲሲ ከፍተኛ የክትባት ደረጃ ካላቸው አምስት ሀገራት አንዷ ነች ነው የተባለው፡፡

በአህጉሪቱ ሲዲሲ እስካሁን ባለው መረጃ 39 ሀገራት ስለ ኦሚክሮን ስርጭት አሁናዊ ሁኔታ ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፥ ካደረጉት ሪፖርት በመነሳት ስርጭቱ ከገና በአል በኋላ በተፈጠረው የሰዎች ንክኪ የቁጥር መጨመር ማሳየቱን ገልጽዋል፡፡

በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ስለ ቫይረሱ ስርጭት እና አጠቃላይ ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል የተሟላ መረጃ ስለሌለ ስርጭቱ በምን ሁኔታ እየተስፋፋ እንደሆነ እና ምን ጉዳት እንዳስከተለ ለማወቅ መቸገሩን
የአፍሪካ የሲዲሲ አስታውቋል።

መረጃው እንደሚያሳየው በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10 ሚሊየን በላይ በላይ መድረሱን ኤስ ኤ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.