Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ለጉባኤ በመጡ ተሳታፊዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የማጣራት ምርመራ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት ለጉባኤ በመጡ ተሳታፊዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የማጣራት ምርመራ እያካሄደ ነው።

ዛሬ በህብረቱ ዋና ፅህፈት ቤት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚካሄደው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተጀምሯል።

ይህንንም ተከትሎ ለጉባኤው የመጡ ተሳታፊዎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከመግባታቸው በፊት የኮሮና ቫይረስ የማጣራት ምርመራ በማከናወን ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ የኖቭል ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ላይ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች።

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና 27 የተለያዩ የድንበር መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ የማጣራት ምርመራ በተጠናከረ ሁኔታ እየተከናወነ ነው።

የማጣራት ምርመራው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያላቸውን ሰዎች የሚለይ ሲሆን፥ ይሄም የቫይረሱ የበሽታ ምልክት የሚያሳዩትን ለመለየት ይረዳል።

የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፥ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ በመሪዎች ደረጃ ይካሄዳል።

በስላባት ማናዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.