Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤውን ከዛሬ ጀምሮ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ግንቦት 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤውን ከዛሬ ጀምሮ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ያካሂዳል፡፡
ከግንቦት 25 እስከ 28 በሚካሄደው ስብሰባ የህብረቱ መሪዎች በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመጀመሪያ ህብረቱ በአህገሪቱ ስላለው የሰብዓዊ ጉዳይ በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን÷በመቀጠልም ሽበርተኝነትን እና በአፍሪካ የሚስተዋለውን ህገ መንግስታዊ ያልሆነ የመንግስት ለውጥ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
ህብረቱ ወቅታዊውን የሰብዓዊ ተግዳሮት በመለየት የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማደረግ እንዲሁም ከግጭት በኋላ በማገገም ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ተጠቁሟል፡፡
አፍሪካ እያጋጠሟት ያሉትን ወቅታዊ የሰብዓዊ ተግዳሮቶች ለመፍታት ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያስከተላቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖችን ለመግታት እንዲሆም የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመቋቋም ህብረቱ ምክክር በማድረግ ዘላቂ መፍትሄዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በመድረኩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት÷ ህብረቱ የተከሰቱ የሽብርተኝነት እና ፅንፈኝነትን ለመዋጋት የተወሰዱ ርምጃዎችን እና በአፍሪካ የሚስተዋለውን ኢ-ህገ መንገስታዊ የመንግስት ለውጥ በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡
የመሪዎች ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ ሚኒስትሮች፣የተለያዩ ሃገራት መሪዎች እንዲሁም ሌሎች ዲፐሎማቶች ይሳተፋሉ መባሉን ከህብረቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.