Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት 36ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ህብረት 36ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል።

በአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ መካሄድ በጀመረው ጉባዔ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማትን ጨምሮ የ55 የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ነው።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር የሆነችው ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ በንግግራቸው፥ በርካታ ችግሮች የተደቀኑባትን የጦር መሳሪያ ድምፅ የማይሰማበት አፍሪካን የመፍጠር ፕሮጀክት ይሳካ ዘንድ ሁሉም አባል ሃገራት ትብብር እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ በንግግራቸው፥ በርካታ ችግሮች የተደቀኑባትን የጦር መሳሪያ ድምፅ የማይሰማበት አፍሪካን የመፍጠር ፕሮጀክት ይሳካ ዘንድ ሁሉም አባል ሃገራት ትብብር እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀ መንበሩ አክለውም ከግጭቶች ጋር ተያይዘው ለሚፈጠሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አስፈላጊ መፍትሄ እንዲሰጥ እና ለስደተኞች አስፈላጊው ጥበቃ እና እንክብካቤ ሊደረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

አያይዘውም የአፍሪካ ህብረት የማሻሸሻያ ስራዎች እና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝም ነው ያስታወቁት።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንጌ በበኩላቸው፥ ማቆሚያ ያጣውን ግጭቶች የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት እየጎዳው ነው ብለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ዋና ፀሐፊ ቬራ ሶንጌ በበኩላቸው፥ ማቆሚያ ያጣውን ግጭቶች የአህጉሪቱን ምጣኔ ሀብት እየጎዳው ነው ብለዋል።

በዛሬው እለት የተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ጉባኤ እስከ ነገ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

ሚኒስትሮቹ በስብሰባቸው በአፍሪካ ህብረት ቋሚ መልዕክተኞች ባረቀቁት የመሪዎች ጉባዔ አጀንዳ ላይ ከተወያዩ በኋላ ለመሪዎቹ ጉባዔ እንዲቀርብ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ህብረት መሪዎች 33ኛ መደበኛ ጉባኤ የካቲት 1 እና 2 2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።

የመሪዎቹ ጉባዔ “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት”በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድም ተነግሯል።

በጉባዔው ላይ የ31 የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች፣ 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የ7 ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የ3 ሃገራት ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ 14 ቀዳማዊት እመቤቶችን ጨምሮ 45 ሀገራት በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ ነው የሚጠበቀው።

ከአባል ሀገራት ውጭም የካናዳ እና የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ የፍልስጤም መሪ፣ የሶስት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የሰባት ሀገራት አምባሳደሮች ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

በአጠቃላይ በጉባኤው 10 ሺህ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው የተገለፀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.