Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማት የ10 ሚሊዮን ዶላር ብድር  ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 1፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማት የ10 ሚሊዮን ዶላር ብድር   መፍቀዱን አስታወቀ።

በረጅም ጊዜ የሚከፈለው ይህ ብድር  በቱሉ ሞዮ አካባቢ ለሚገነባው የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑም ነው የተገለጸው።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በታዳሽና በፍጥነት ጥቅም ላይ በሚውል የኃይል አቅርቦት ታግዛ ኢኮኖሚዋንና የሕዝቧን አኗኗር ያሻሽላል ተብሎ  ታምኖበታል።

በኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ቴክኖሎጂ የመጀመሪያው የእንፋሎት ኃይል አምራች እንደሚሆንም ነው ባንኩ የገለጸው።

በአፍሪካ ልማት ባንክ የአየር ፀባይ ለውጥና የአረንጓዴ እድገት ዳይሬክተር አንቶኒ ኒዮንግ ÷“የታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂ ፈንድ በዚህ ፕሮጀክት በመሳተፉ ደስተኛ ነኝ፣በረጅም ጊዜ ክፍያ የተፈቀደው ብድር አገሪቱ የኃይል አቅርቦት አማራጯን እንድታሰፋ ያግዛታል ”ብለዋል።

ከዚያም ባለፈ አገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ የያዘችውን ግብ እንድታሳካ ያስችላታልም ነው ያሉት።

ፕሮጀክቱ የ 50 ሜጋዋት የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ዲዛይን፣ ግንባታ ፣የሙከራ ሂደት፣የኃይል አቅርቦት ስርጭትና ማስተላለፍ ተግባራት  እንደሚከናወኑበትም ነው የተገለጸው።

ከዚያም ባለፈ 11 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የማስተላለፊያ መሥመር እንደሚዘረጋለትም ተመላክቷል።

በአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና የኢንቨስትመንት ኦፊሰርና የታዳሽ ኃይል ስፔሻሊስት አንቶኒ ካሬምቦ  በበኩላቸው ÷ ፕሮጀክቱ አረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋትና ለ600 ሰዎች የሥራ  እድል ይፈጥራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.