Fana: At a Speed of Life!

ተምች በጅማ ዞን ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተምች በጅማ ዞን በሸቤ ሰምቦ ወረዳ መከሰቱን የጅማ እፅዋት ክሊኒክ ማዕከል አስታውቋል፡፡

የማዕከሉ ሀላፊ አቶ ቦና ሂርጳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ተምቹ በወረዳው በሚገኙ አራት ቀበሌዎች ተከስቷል።

በዚህም በ400 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ የበቆሎ፣ጤፍ፣ማሽላ፣ ዳጉሳ እና የግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ ተባዮችና የዕፅዋት በሽታዎች እየተስፋፉ በመሆኑ አርሶ አደሩ ማሳውን በመፈተሽ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በተመስገን አለባቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.