Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አህጉራዊ  ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ ያተኮረ ውይይት በበይነ መረብ ተካሂዷል።

በውይይቱ በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሀደራ አበራ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነትና ድርድር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ሙሴ ምንዳዬ እንዲሁም የውጭ ንግድ እና ቱሪዝም ማስፋፊያ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ተረፈ ዲዳ እና ሌሎች ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

አቶ ሙሴ ምንዳዬ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና መመስረት ያስፈለገበት ዋና ዓላማ፣ አባል መሆን የሚያስገኛቸው ጥቅሞችና የሚፈጥራቸው አሉታዊ ተጽዕኖዎች፣ ሀገራችንም በዚሁ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተቱ የምትፈልጋቸውን ዕቃዎች ዝርዝር አዘጋጅቶ የማቅረብ ሂደትን እያጠናቀቀች መሆኑን እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሀደራ አበራ ጋና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ትግበራ ተጠቀሚነቷን ከፍ ለማድረግ ያለውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ገለጻ አቅርበዋል።

በዚህም ቅድመ ዝጅጅት አደረጃጀት ከማስተካከል ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ከመስራት፣  እና ወደ ተለያዩ ሀገራት የንግድ ልዑካን ቡድን ከመላክና ተመሳሳይ የልዑካን ቡድን ወደ ሀገራቸውም በመጋበዝ የተደረጉ የዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴዎች አኳያ በተጨማሪ ሰባት ዓይነት የውጭ ንግድ ምርት ዘርፎች ለይተውና ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

ከገለጻው በኋላም ተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በመስጠት  ሰፊ ውይይት መደረጉን  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.