Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባዔ ለመታደም አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ በሚካሄደዉ 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባዔ ለመታደም የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፣የኮትዲቯር ሪፐብሊክ፣ የጋቦን እና የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሮቹን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ፋይሰል አሊይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በስብሰባው ለመሳተፍ የላይቤሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ኬማያ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።

39ኛው የኅብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔ ለሁለት ቀናት “ጥበብ፣ ባህልና ቅርስን የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት እንጠቀም” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሕብረቱ 55 አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.