Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮረ አህጉራዊ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አራት የአህጉሪቱ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡
ኮንፈረሱ አፍሪካውያን ጋዜጠኞች በምርመራ ጋዜጠኝነት ልምድ የሚለዋወጡበት እና የሚሰለጥኑበት ነው።
በአዲስ አበባ፣ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ፣ በሴኔጋል ዳካር፣ በናይጄሪያ አቡጃ እና በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ጋዜጠኞች በየቀጠናው እየተሳተፉ ነው።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን ኮንፈረንስ አይ ኤም ኤስ ፎጆ (IMS –FOJO) ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዊውተርስራንድ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
የአይ ኤም ኤስ ፎጆ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ሶፊ ጉልልበርግ ኮንፈረንሱ በአፍሪካ የምርመራ ጋዜጠኞችን አቅም በስልጠና ለማዳበር የተዘጋጀ ነው ብለዋል።
በአህጉሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞች ስለ ምርመራ ጋዜጠኝነት አሰራር እና አካሄድ ልምድ እንዲለዋወጡ ያለመ እንደሆነም ገልጸዋል።
በኮንፈረሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የምርመራ ዘገባዎችን የሰሩ ጋዜጠኞች ልምዳቸውን እያጋሩ ነው።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ኮንፈረንስ ከመገናኛ ብዙሃን ተቋማት የተውጣጡ ጋዜጠኞች እና የዩንቨርስቲ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል።
በአልአዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.