Fana: At a Speed of Life!

የኢራቅ ፓርላማ የአሜሪካ ወታደሮች ከኢራቅ እንዲወጡ የሚያስችል ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢራቅ ፓርላማ በሀገሪቱ የሚገኙ የውጭ ሀገራት ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚያስችል ውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ፡፡

ይህ ውሳኔ የመጣው የኢራን ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሴም ቃሴም ሱለይማኒ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን መገደላቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ፓርላማው የውጭ ሀገር ወታደሮች የሀገሪቱን መሬት ፣ የአየር ክልል እንዲሁም የውሃ ክልል ለምንም አይነት ምክንያት እንዳይጠቀሙ  አግዷል፡፡

በአሁን ወቅት  በኢራቅ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በድጋፍ ሰጪነት የተሰማሩ ናቸው፡፡

ይህ የፓርላማው ውሳኔ የተላለፈው የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አዴል አብዱል ማሃዲ በኢራቅ የሚገኙ የውጭ ሀገራት ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ለፓርላመው ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን የወታዳራዊ መሪያቸውን ቃሴም ሱለይማኒን አስክሬን አደባባይ በመውጣት ተቀብለዋል፡፡

አስክሬኑን በተቀበሉበት ወቅት ኢራናዊያኑ ደረታቸውን እየመቱ ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን  ሞት ለአሜሪካ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

ቃሴም ሶሊማኒ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ለፈጠረችው ተፅዕኖ ከፍ ያሉ አስተዋፅኦ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን በኢራን ሁለተኛ ከፍተኛ ሀይል( ስልጣን) እንደነበሩም ይገመታል፡፡

ምንጭ፤-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.