Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ ጉዳዮች እና በአቅም ግንባታ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ ጉዳዮች እና በአቅም ግንባታ መስኮች በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከደቡብ ሱዳን የውስጥ መረጃ ቢሮ ዳይሬክተር ጀነራል አኮል ኮር ኩክ ጋር በዛሬው ዕለት በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኤፍቢሲ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአካባቢያዊ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የነበራቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።

በተለይ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን፣ ሽብርተኝነትንና በድንበር አካባቢ የሚታዩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ቀጣናዊ ሰላምንና ደህንነትን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን የደህንነት ተቋማት በአቅም ግንባታ መስኮች በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የጠቆመው መግለጫው፤ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር በሚገኘው ብሄራዊ የመረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አማካኝነት  ለደቡብ ሱዳን ባለሙያዎች ስልጠናዎች ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.