Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነት ለመጠበቅ የመከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና አንድነት ለመጠበቅ መከላከያ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ የጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡

በምዕራብ እዝ 22ኛ ንስር ክፍለጦር የእውቅና መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

ሰራዊቱ የድል ምልክት ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፥ አሁንም ኢትዮጵያን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል።

22ኛ ንስር ክፍለ ጦርም በርካታ ድሎችን በተለያዩ አውደውጊያዎች መፈፀሙን ነው የተናገሩት።

የክፍለ ጦሩ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ሰይፈ ኢንጌ ክፍሉ በቤንሻጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱት አሸባሪው ሸኔና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ላይ የተጠናከረ እርምጃ በመውሰድ ውጤት ማስመዝገቡን አንስተዋል።

በክፍለ ጦሩ የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው የሰራዊቱ አባላትም የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸው በክልሉ ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ መከላከያ ሰራዊቱ ቁልፍ ሚና ነበረው ብለዋል።

በተመሳሳይ መከላከያ ሰራዊት ሀገር ለማስቀጠል በመስዕዋትነት ያስመዘገባቸው ድሎች ታሪክ የሚዘክራቸው ናቸው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገልጸዋል፡፡

አቶ አሻድሊ ክልሉ በህግ ማስከበርና የክልሉን ሰላም በማስጠበቅ ለተሳተፉ የፀጥታ አካላት የእውቅና መርሐ ግብር ባዘጋጀበት ጊዜ እንደተናገሩት ÷ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል የተሸረቡ ሴራዎች በፀጥታ ሃይሎች የጋራ ገድል ከሽፈዋል።

መከላከያ ሰራዊት ሀገር ለማስቀጠል በመስዕዋትነት ያስመዘገባቸው ድሎች ታሪክ የሚዘክራቸው ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷የክልሉን ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡

በክልሉ የጠላትን ተልዕኮ በመቀበል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች እጃቸውን በሰላማዊ መንገድ በመስጠት ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲቀጥሉም አቶ አሻድሊ ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አቢዮት አልቦሮ  በበኩላቸው ÷መርሐ ግብሩ ለተገኘው አንፃራዊ ሰላም እውቅና ለመስጠትና የግዳጅ ዝግጁነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ:-

https://www.youtube.com/watch?v=vZRr-XdLuTg

የመከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያን ለመበተን የተነሱ ክፉዎችን ህልም ያከሸፈ የቁርጥ ቀን ልጅ እንደሆነም አንስተዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.