Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ለመደገፍ የሚውል የ6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ያለውን የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ለመደገፍ ብሪታኒያ እና ጀርመን 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።

ሁለቱ ሀገራት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ይፋ ያደረጉት ድጋፍ በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው በርካታ ሰዎች በስራቸው እንዲቀጥሉ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከኮሮና ቫይረስ

ተፅዕኖ እንዲያገግም ለማገዝ ይረዳል ነው የተባለው።

በዚህም የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች የደመወዝ ማካካሻ እንዲያደርጉ እና የኮሮና ቫይረስ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለሚቋቋሙ የንግድ ተቋማት ሽልማት እንደሚበረከትም ተጠቁሟል።

ድጋፉ በትናንትናው ዕለት ይፋ ሲሆን በቀጣይ ወራትም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ቮይስ ኦንላይን ዘግቧል።

የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ከማምረቻ ዘርፉ ቀዳሚው የስራ እድል ፈጣሪ መሆኑን የፌደራል ስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታውቀዋል።

ነገር ግን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የፍላጎት መቀነስ መስተዋሉ ዘርፉን በከፍተኛ ሀኔታ ሊጎዳ ይችላል ተብሏል።

በቀጣዮቹ ሶስት ወራት በኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 4 እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን የስራ እድሎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ግምቱን አስቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.