Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ነው፡፡
ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ማድረግ መጀመሩን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡
ዛሬ ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር እየተደረገ ያለው ምክክር የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው÷ የምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እየሄደበት ስላለው ቅድመ ዝግጅትና ትግበራም ገላጻ አድርገዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር ስለሚኖረው የአጋርነት ስራ ውይይት ላይ እንደተገለጸው፥ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶችን አጥብቦ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያለመው ኮሚሽኑ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ትግበራ የተለያዩ ክንውኖችን በመፈጸም ላይ ይገኛል።
በቅድመ ዝግጅት ክንውኑም ከውስጥ አደረጃጀቱ ትውውቅና ልዩ ልዩ ምክክሮች ባሻገር ከተቋማት ግብአቶችን መውሰዱ ተገልጿል።
በዛሬው መድረኩም ከመገናኛ ብዙኃን ጋር በምን መልኩ ተቀራርቦ መስራት እንደሚቻል የልምድ ልውውጥ በማድረግ ላይ ይገኛል።
በዝግጅት ምዕራፍ ውስጥ አጀንዳ የሚሰበሰብበትን መርህ፣ ሕገ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ስትራቴጂዎችን የማዘጋጀት፣ የክልል ጽሕፈት ቤቶችን ማደራጀትና መምራት፣ አጀንዳ ለማሰባሰብ ስራዎችን ለመስራት በሂደት ላይ ይገኛልም ተብሏል።
በተስፋዬ ከበደ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.