Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሃገር ሉዓላዊነት እና የህዝብ አንድነት ላይ የሚቃጡ ድርጊቶችን እንደማይታገስ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታን በተመለከተ የአቋም መግለጫ ሰጥቷል።
በአቋም መግለጫው ÷ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለልተኛ ቢሆንም በሃገር ሉዓላዊነት እና የህዝብ አንድነት ላይ የሚቃጡ ድርጊቶችን እንደማይታገስ ተቀምጧል ።
በሃገሪቱ ግጭት እንዳይከሰት የአባቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ እና የማወያየት ሙከራቸው በአጥፊው ቡድን እምቢተኝነት አለመሳካቱም ተገልጿል።
በዚህም አሁን ላይ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ግልፅ ጫናዎችን ቀይ መስመር ሲታለፍ ዝም እንደማይልም አስታውቋል።
በጉባኤው በኩል ከበላይ አባቶች በቀረበው ጥሪ እና የአቋም መግለጫ÷ በሃገሪቱ በተከሰተው ቀውስ የዜጎች ህይወት መጥፋቱን፣ ቤተ እምነቶች እና ንብረት መውደሙን ገልፆ ÷ይህ የሃገር ጉዳት ግድ የማይላቸው አንዳንድ የምዕራባውያን ሃገራት በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያለውን ጫና ጉባዔው በመግለጫው አንስቷል።
የአቋም መግለጫው አላማ በኢትዮጵያ ዘለቄታዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፅናት እንዲቆም፣ በኢትዮጵያ ላይ እኩይ ዘመቻዎች እና ጫናዎችን የሚያሳድሩ ሃገራት፣ ተቋማት እና ሚዲያዎች ከአፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ የአቋም መግለጫ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፣ ለአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለኤምባሲዎች እና ለተለያዩ አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት እና ድርጅቶች በተለያዩ ቋንቋዎች እንደሚላክ ጉባዔው አስታውቋል።
በፍሬህይወት ሰፊው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.