Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አክሱምንና አድዋን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አክሱምንና አድዋን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም የአዲግራትን ዙሪያ መቆጣጠሩን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡

በምዕራብ ግንባር የሕወሓት ጁንታን ኃይል እያጠቃ ያለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሓት ኃይል ገጥሞት ነበር ተብሏል።

ሰለህለሃ ላይ የመሸገው የጁንታው ኃይል መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከል አድርጓል ነው የተባለው።

የመከላከያ ሰራዊቱ የጁንታውን ተከላካይ ኃይል ሰብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ተገልጿል።

ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሰራዊቱ ድል ማድረጉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ገልጿል።

የመከላከያ ሰራዊቱ እንቲጮንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል።

አያሌ የጁንታው ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከድተው ከጁንታው ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም ይገኙበታል ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.