Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ10 ወራት ውስጥ 36 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን አገበያየ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2013 በጀት ዓመት አስር ወራት 569 ሺህ 767 ሜትሪክ ቶን ምርት በ36 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ማገበያየቱን አስታወቀ።

አጠቃላይ ግብይቱ የእቅዱን በመጠን 101 በመቶ በዋጋ 107 በመቶ ይሸፍናል ተብሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከተገበያየው ምርት መጠን ውስጥ ውስጥ ቡና 35 በመቶ፣ ሰሊጥ 32 በመቶ፤ አኩሪ አተር 14 በመቶ፤ ቀይና ዥንጉርጉር ቦሎቄዎች ሰባት በመቶና ነጭ ቦሎቄ አምስት በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡

በእነዚህ 10 ወራት 201 ሺህ 401 ቶን ቡና ለግብይት ቀርቦ በ21 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር፤ እንዲሁም 183 ሺህ 299 ቶን ሰሊጥ በ9 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ለመገበያየት መቻሉን ከምርት ገበያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪም 33 ሺህ 959 ቶን ነጭ ቦሎቄ በ871 ሚሊየን ብር፣ 79 ሺህ 951 ቶን አኩሪ አተር 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር፣ 29 ሺህ 71 ቶን አረንጓዴ ማሾ በ1ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ግብይታቸው ተፈፅሟል።

በተለይ በዚህ ዓመት ወደ ግብይት ሥርዓቱ የገቡት ዥንጉርጉር ቦሎቄዎች 41 ሺህ 374 ቶን ለግብይት ቀርቦ በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ተገበያይቷል ተብሏል።

የኢትዮጵያን የማዕድን ምርቶች ለማገበያየት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት ለመቀየስ  ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ጋር  የመግባባቢያ ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል።

ይህንን ለማሳካትም የሁለቱ መስሪያ ቤቶች ባለሙያዎች ያለበት የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ተጠቁሟል።

እንዲሁም ዘይት አምራች የግብርና ምርት አቀነባባሪ ኢንዱስትሪዎች ለግብዓት የሚጠቀሙበትን አኩሪ አተር ከዘመናዊ ግብይት ስርዓቱ ማግኘት የሚችሉበት አዲስ የገብይት መስኮት  ከተከፈተበት ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓም አንስቶ 25 አቀናባሪዎች 39 ሺህ 886 ሜትሪክ ቶን ምርት በ888 ሚሊየን ብር ማገበያየት መቻሉ ነው የተነገረው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.