Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሰራዊት እያለ ኢትዮጵያ አትደፈርም – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰራዊት እያለ ኢትዮጵያ አትደፈርም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምዕራብ ግንባር የሚገኙ የሰራዊት አባላትን ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ሰራዊት እያለ ኢትዮጵያ አትደፈርም ብለዋል።

የሰራዋቱ የጀግንነት ምስጢር ድል የሚፈጥር መሆኑ፣ ከመሬት በላይ ለትውልድ የሚተላለፍ ስም ተክሎ ሞትን ማሸነፉ፣ ለድንገተኛ ክስተት የማይበገር፣ ፍላጎቱን ለዓላማ ያስገዛ መሆኑን አንስተዋል።

አያይዘውም የነጻነትን ዋጋ ማወቁ ፣ ጨለማን ወደ ብርሀን የሚቀይር ጉልበት ስላለው እና በልማትና ጥፋት መካከል የማይፈርስ ጠንካራ ግንብ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ይህ ጀግና ትውልድ የኢትዮጵያን ክብር ጠብቆ ለሚቀጥለው የበለጸገች ሀገር ያስረክባልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ጠላቶቻችን አንገቶቻቸውን ይደፋሉ ለዚህ የሚከፈል ማንኛውም መስዋዕትነት ክብር መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “ዛሬ በምዕራብ ግንባር ተገኝቼ ያየሁት የሠራዊቱ ወትሮ ዝግጁነት እጅግ አስደናቂ ነበር። ኢትዮጵያን ከማንም፣ በምንም ሁኔታና መቼም ሉዓላዊነቷን ለማስከበር፤ ሁለንተናዊ ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ሠራዊት ወሳኝ ነው። በምዕራብ ግንባር ያየነውም ይሄንን ነው” ብለዋል።

በአልአዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.