Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ሠራተኞች በደብረብርሃን ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስታትስቲክስ አገልግሎት አመራሮችና ሠራተኞች ከሰሜንና ደቡብ ወሎ ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ባደረሰው የሽብር ጥቃት ተፈናቅለው ደብረብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ከ2 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ድጋፍ ያደረገው የኢትዮጵያ እስታትስቲክስ አገልግሎት ÷ የእለት ደራሽ ምግቦች፣ የሴቶች የንጽሀና መጠበቂያ ቁሳቁሶችና የተለያዩ አልባሳትን ለሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከለከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት አስረክቧል፡፡

የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት አበራሽ ታሪኩ እንደተናገሩት ÷ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞችና አመራሮች የተበረከተውን ጨምሮ እስካሁን ከ11 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ሰራተኞችም ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ደም በመለገስ ጭምር አጋርነታቸውን አሳይተዋል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ÷ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥልም ነው የተናገሩት፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የዞኑ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበባው መሰለ በበኩላቸው÷ የተበረከተውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች በአግባቡ እናደርሰለን ብለዋል፡፡

ታለ ማሞ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.