Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ በመጪው 2013 አገራዊ ምርጫ የመወዳደሪያ ማኑፌስቶውን አስተዋወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ/ኢሶዴፓ/ በመጪው 2013 አገራዊ ምርጫ የመወዳደሪያ ማኑፌስቶውን አስተዋውቋል፡፡

ፓርቲው በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ በሚከተላቸው 21 አገራዊ የፖሊሲ አቅጣጫዋዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በዚህም የህዝቦች አንድነት የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ እና አገራዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ ረገድ በማንኛውም ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም እንደሚያስቀድም አስታውቋል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት ለማድረግ ጉዳዮን ወደ ድርድር እንደሚያመጣው ፓርቲው ገልጿል፡፡

ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በማንኛውም የአገሪቱ ክልሎች በነፃነት የመስራት፣ የመኖር እና የመምረጥ መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር እንደሚያደርግ አመልክቷል፡፡

በክልሎች ካለው የፀጥታ መዋቅር አንፃር ልዮ ሀይል ኢ-ህገመንግስታዊ በመሆኑና አገርን ወደ መከፋፈልና መበታተን ያሚያመራ በመሆኑ ችግሩን እንዲስተካል በትኩረት እንደሚሰራ ፓርቲው ጠቅሷል፡፡

በአገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመንግስት ተሳትፎ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ የሚሰራበት ሁኔታ እንደሚፈጥር ጠቁሟል፡፡

በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፎች በርካታ የሰው ሀይል የሚቀጥር ሆኖ ለዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር እንደሚሰራ ፓርቲው በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

የአምባሳደርነት ሞያ ለመንግስት ሃላፊዎች በችሮታ የሚሰጥ ሳይሆን ችሎታን ማዕከል አድርጎ እንዲፀድቅ ይደረጋል ብሏል፡፡

ሁሉም ዜጋ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስድ በማድረግ አስፈላጊ ለሆነ አገራዊ ግዴታ የራሱን ሚና መወጣት እንዲችል ይሰራል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የምርጫ ምልክትም የእጅ ባትሪ መሆኑን በመግለጫው መጠቀሱን ኢብኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.