Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በተደረገ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን አቻው 4 ለ1 ተሸነፈ፡፡

በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከካሜሩን አቻው ጋር አድርጓል፡፡

በዚህም ዋልያዎቹ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ ቢያጠናቅቁም በሁለተኛው አጋማሽ በተቆጠረባቸው ሶስት ጎሎች 4 ለ1 በሆነ ውጤት ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል፡፡

ዋልያዎቹ ባሳለፍነው እሁድ በምድቡ የመጀመሪያው ጨዋታቸው 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በኬፕ ቨርዴ መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.