Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ፡፡
 
ብሔራዊ ቡድኑ የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣት ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ የአፍሪካ ዋንጫን የተቀላለቀለው፡፡
 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ከኮትዲቯር አቻው ጋር ያደረገው ጨዋታ ተቋርጧል፡፡
 
ጨዋታው ዳኛው ድንገት በህመም ምክንያት ሜዳ ላይ በመውደቁ ነው የተቋረጠው፡፡
 

81ኛው ደቂቃ ላይ የተቋረጠው የኢትዮጵያና የኮትዲቯር ጨዋታ የተጎዱትን ዳኛ በመስመር ዳኛ በመተካት ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ የቀጠለ ሲሆን ቀሪ ዘጠኝ ደቂቃዎችን ተጫውተው ውጤቱ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የተመለሰው ከስምንት ዓመታት በኋላ ነው፡፡
 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.