Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 10 ሺህ የሚጠጉ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 ሺህ የሚጠጉ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ማስረከቡን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
በርክክብ ስነሥርዓቱ ላይ የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሃ ይታገሱ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፍስሃ ይታገሱ ባደረጉት ንግግር÷ ኢቢሲ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የመጻሕፍት ማሰባሰብ እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
የተሰባሰቡት መጻሕፍትም ለቤተ መጻሕፍቱ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ያላቸውን እምነት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
መጻሕፍቱ ከድርጅቱ ሠራተኞች እና ከሌሎች ተቋማት የተገኙ መሆናቸውንም ነው አቶ ፍስሃ የተናገሩት፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ ድርጅቱ ለቤተ መጻሕፍቱ እያደረገ ያለው የማስተዋወቅ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአዲስ አበባ ለተገነባው የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በሀገር አቀፍ ደረጃ የ1 ሚሊየን መጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.