Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የISO/IEC 17025 ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በፍተሻ ላቦራቶሪ የISO/IEC 17025 ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ፡፡
ዛሬ በተካሄደው 10ኛው ዓለም አቀፍ አውደጥናት ላይ የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ንጉሱ ክብሩ እንደገለጹት፥ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የአክሪዲቴሽን አገልግሎት እውቅና ማግኘቱ በፊዚካልና ኬሚካል ፍተሻዎች ተረጋግጧል፡፡
የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎች በተጨማሪ÷ በክልሉ ለሚገኙ እና በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ለሚያመርቷቸው ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲመረቱ ተአማኒነትና ተቀባይነት ያለው የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት በመስጠት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ማለታቸውን ከኢንስቲቲዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.