Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ የዋጋ ማሻሻያ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2013(ኤፍ በ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ የዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

ባንኩ ማሻሻያ ያደረገው በብድር ወለድ ምጣኔና በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶቹ ላይ ነው።

የዋጋ ማሻሻያውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ በባንኩ ገቢና ወጪ ላይ የተከሰተውን መዛባት ለማስተካከል፣ ባንኩ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ፣ በዝቅተኛ ዋጋ ወይም በነፃ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ አነስተኛ ማስተካከያ ለማድረግ፣ እና ከገበያው ሁኔታ ጋር ለማቀራረብ በአብዛኛው የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ከ1 በመቶ ያልበለጠ የወለድ ምጣኔ መጨመር የሚያስችለውን የዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የብድር ወለድ ምጣኔ መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገው ብድሮችን በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ገደብ በመከፋፈል እና ባንኩ የሚሰጣቸው የአገልግሎት አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አቶ አቤ ሳኖ በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

የወጪ ንግድ የአጭር ጊዜ አገልግሎቶች ላይ መጠነኛ ጭማሪ ብቻ ተደርጎ፤ የረጅም ጊዜ አገልግሎቶች ዋጋ ደግሞ ባለበት እንዲቀጥል መደረጉንም ገልፀዋል፡፡

የወጪ ንግድን ለማበረታታት ከወጪ ንግድ ጋር የተያያዙ የብድር አገልግሎቶቹ ላይ ሲያስከፍለው በነበረው የወለድ ምጣኔ ላይ እንዲሁም መንግስት ለሚያስመጣው መድሀኒት የሚቀርበው የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ተመን ላይ ቅናሽ መደረጉም ነው በመግለጫው የተገለፀው፡፡

ህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማስቀረት ባንኩ ለነዳጅ የሚያቀርበው የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት ተመን ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የገለጹት አቶ አቤ፤ ሌሎች በመንግስት የሚሠሩ ሥራዎች የአገልግሎት ዋጋ ላይ አነስተኛ ጭማሬ ብቻ መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

የባንኩን ውጤታማነት ለማስቀጠልና ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ለማሳደግ የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፤ ባንኩ እስካሁን ከመደበኛ አገልግሎት የሚያገኘው 27 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፤ ከ73 በመቶ በላይ በነፃ እና በዝቅተኛ ዋጋ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።

እስካሁን በነበረው አሰራር ባንኩ ዝቅተኛ ዋጋ በማስከፈል አገልግሎት መስጠቱ ገበያን በማዛባት፣ ሃብት በማባከን፣ ፕሮጀክቶች በጊዜ እንዳይጠናቀቁ፣ በብድር አከፋፈል በኩልም ዳተኝነትን ማሳየትና ጥገኝነትን የሚያበረታታ ነውም ተብሏል።

ባንኩ መንግስታዊ ከመሆኑ አንፃር ዋጋ የማረጋጋት ኃላፊነት እንዳለበት የገለጹት አቶ አቤ፤ አሁን የተደረገው አነስተኛ የዋጋ ማስተካከያ ህብረተሰቡ ላይ ጫና በማያሳርፍ መልኩ እና የባንኩን ህልውና በሚያስጠብቅ መልኩ እንዲሆን መደረጉን ማስረዳታቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.