Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚያዝያ 01 እስከ ሚያዝያ 03 የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚያዝያ 01 እስከ ሚያዝያ 03 2012 ዓ.ም የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ገለፀ።

ባንኩ በፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው፥ የባንኩን የኮር ባንኪንግ ቴክኖሎጂ አቅም ማስፋፊያ ስራውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ከመጪው ሐሙስ ሚያዝያ 01 ቀን እስከ ቅዳሜ ሚያዝያ 03 ቀን 2012 ዓ.ም. ሙሉ ቀን አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የሞባይል እና ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት በተጠቀሱት ቀናት እንደማይኖሩም ነው ባንኩ የገለፀው።

ይሁን እንጂ የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎት በማይሰጡባቸው በእነዚህ ቀናት ሁሉም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ ኤም ማሽኖች፣ ፖስና ሲቢኢ ብር የተለመደውን አገልግሎት እንደሚሰጡም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.