Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ በርበራ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ የሶማሌላንድ የወደብ ከተማ በርበራ ከየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።
አየር መንገዱ ወደ በርበራ በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራ ለማድረግ እቅድ እንዳለውና ወደፊት የበረራ ቁጥሩን እንደሚጨምርም አስታውቋል።
በረራው አየር መንገዱ በአፍሪካ ያለውን መዳረሻ ወደ 43 እንደሚያሳድግለት የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ 19 በመቶ ድርሻ ያላት ሲሆን በወደቡ ላይ መርከቦቿን ከወራት በፊት ማሰማራት ጀምራለች።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of outdoors and text
0
People reached
4
Engagements
Distribution score
Boost post
4
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.