Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት ጎን ለጎን ተቋማዊ አደረጃጀቱንም ይበልጥ በማዘመን ላይ ይገኛል – ብ/ጄነራል ነገራ ሌሊሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሀገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት ጎን ለጎን ተቋማዊ አደረጃጀቱንም ይበልጥ በማዘመን ላይ እንደሚገኝ ምክትል አዛዥ ለአየር ሎጂስቲክስ ብርጋዴር ጄነራል ነገራ ሌሊሳ ገለጹ።

ብርጋዴር ጄነራል ነገራ ሌሊሳ ፥ የመንግስትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የመጡና ነዋሪነታቸውን ኔዘርላንድስ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ፥ ተቋሙ ወቅታዊ ቁመናው ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት በሚያስችል ቁመና እና ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የዳያስፖራ አባላቱ በቆይታቸው፥ በቢሾፍቱ ደረጃ 3 የአየር ኃይል ሆስፒታል ለሚገኙት የጦር ጉዳተኞች የምሳ ግብዣ ያደረጉ ሲሆን ፥ ከ500 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ አልባሳትንና የንፅህና መጠበቂያ ስጦታዎችን አበርክተዋል።

ከቡድኑ አባላት መካከል አቶ አቡድልናስር አብደላ አህመድ እና አቶ እዮብ ደምሴ፥ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ መምጣቱንና ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚኮሩበት የጋራ የሆነ ጠንካራ ተቋም እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

የአየር ኃይል ጤና ማዕከል ኃላፊ ኮለኔል ፋንታሁን ተፈራ ፥ የዳያስፖራ አባላቱ ኢትዮጵያዊ አጋርነታቸውን በተግባር ያረጋገጡበት በመሆኑ አመስግነው ፥ ‘‘ይህ በጎ ምግባር ለሠራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነውና ድጋፉ በሌሎችም ሀገር ወዳድ ዜጎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል’’ ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.