Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ።

ስድስተኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን ለማቋቋም ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል።

በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ፥ የረቂቅ አዋጁን መነሻ፣ አስፈላጊነት፣ የያዛቸውን ድንጋጌዎችና ሌሎች ተጨማሪ ሃሳቦችን በተመለከተ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

መሰረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በልሂቃን መካከል የሚስተዋለውን ልዩነትና አለመግባባት በማስተካከል ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህም ምክክሩን የሚመራ አካል በህግ ማቋቋም በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

የአዋጁ መዘጋጀት በተለያየ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ልሂቃን ተቀራራቢና ለአገራዊ አንድነት ገንቢ የሆነ አቋም እንዲይዙ ማድረግ ያስችላልም ነው ያሉት።

የኮሚሽኑን ገለልተኝነት ለማረጋገጥ በረቂቅ አዋጁ የተለያዩ ድንጋጌዎች መካተታቸውን ጠቅሰው የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ የስራ ዘመኑ 3 አመት ሲሆን ስራው ካልተጠናቀቀ በምክር ቤቱ ሊራዘም እንደሚችል መቀመጡን ጠቅሰዋል።

ምክር ቤቱ የረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የተነሱ ሃሳቦችን ጨምሮ በዝርዝር እንዲያየው ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው የመንግስትና የግል ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ በዋናነት ለፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.