Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የንግድ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሃመድ በኢትዮጵያ ከሶማሊያ አምባሳደር አብዱላሂ አህመድ ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ሁለቱ እህትማማች ሃገራት የሚያስተሳስሯቸው በርካታ የንግድ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ፥ ይህንን የጠበቀ ትስስር ወደ ጋራ ተጠቃሚነት መቀየር ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስትም በሃገሪቱ ላይ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓትን በመፍጠር የወጪ ንግድ ግኝትን ለማሳደግ እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሶማሊያ አምባሳደር አብዱላሂ አህመዲን በበኩላቸው፥ የሶማሊያ መንግስት ሁለቱን ሃገራት በንግድ ለማስተሳሰር የሚደረገውን ጥረት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ አቋም አለው ብለዋል፡፡

የሶማሊያ የኮሙኑኬሽን፣ ኢንፎርሜሽን እና ቱሪዝም ሚኒስትር ፕሮፌሰር ኦስማን ዱቤ፥ የሁለቱን እህትማማች ሃገራት ህዝቦች በንግዱ ዘርፍ በማስተሳሰር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሶማሊያ መንግስት እንደሚደግፍና ለተግባራዊነቱም አበክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱን ሃገራት የንግድ ትስስር ለማሳለጥ እና በፍጥነት ወደ ተግበራ ለመግባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋገረው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.