Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሁለት አመራሮች ላይ የእገዳ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከፌዴሬሽኑ ውክልና ሳይሰጣቸው በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ተገኝተው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በመወከል ምርጫ የመረጡ የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲታገዱ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ከሰብሳቢዋ ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙ ባለፈም ሰብሳቢዋ በምርጫው ተወዳዳሪ ሆነው እንዲሳተፉ ከፌዴሬሽኑ እውቅና ውጪ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሳይወስን ማንንም ሳያማክሩ ደብዳቤ የጻፉት የፌዴሬሽኑ ምክትል ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴም ከዛሬ ጀምሮ ለ20 ቀናት ከስራ ታግደው እንዲቆዩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የሴቶች እግር ኳስ ልማት እና ውድድር ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሶፊያ አልማሙ የታገዱት እስከ 13ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.