Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባቶች ከአሜሪካ ኮንግረስ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ ከአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ።
የጳጳሳቱ ከባለስልጣናቱ ጋር መወያየት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን የተዛባ አቋም ለማስተካከል ይረዳል ተብሏል።
ውይይቱን በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙ የ11 አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በዋሽንግተን ዲሲ ከኮንግረንስ አባላት ጋር ተገናኝተው ነው ያደረጉት።
ነገ ደግሞ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኀላፊዎችና ሴናተሮች ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል።
በአሜሪካ ሀገረ ስብከት ያላቸው ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት በአሜሪካ ኮንግረስ በመገኘት የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ሁኔታ መረዳት እንዳለበት ተናግረዋል።
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ጫና እንዲያቆም መጠየቃቸውንም ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
11,108
People Reached
1,287
Engagements
Boost Post
798
38 Comments
60 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.