Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የቡሩንዲ አቻውን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ከቡሩንዲ አቻው ጋር ተጫውቷል።

ቡድኑ የቡሩንዲ አቻውን 2ለ1በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦች ሥራ ይርዳው በ27 ኛው እና አረጋሽ ከልሳ በ30 ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል።

ቡድኑ ፓናማ እና ኮስታሪካ በጥምረት በሚያዘጋጁት የ2020 ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ውድድር ነው ከቡሩንዲ ጋር የደርሦ መልስ ጨዋታውን ያካሄደው።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከሁለት ሳምንታት በፊት በመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያው ወደ ቡጁምቡራ በማቅናት 5 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል።

የዛሬው ጨዋታ 2ለ1 መጠናቀቁን ተከትሎም በደርሦ መልስ 7ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለው ቡድኑ በቀጣይ ከማላዊ እና ዚምባብዌ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.