Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 21 ፡ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

በምግብ ደህንነት ስራ አመራር ትግበራ ላይ የምክር አገልግሎት ለመስጠት ፑራቶል ኢትዮጵያ የምግብ ኢንዱስትሪ ከተባለ ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳለው መኮንን እና ፑራቶል ኢትዮጵያ የምግብ ኢንዱስትሪ ዋና ዳይሬክተር ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን አፈፃፀሙን በመገምገም እየተሻሻለ እንደሚሄድ መገለጹን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.