Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት 400 የምርትና የአገልግሎት ደረጃዎችን በብሔራዊ የደረጃዎች ምክርቤት አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደረጃዎችኢንስቲትዩትያዘጋጀቸውን 400 የምርትና የአገልግሎት ደረጃዎችን በብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት ማፀደቁን አስታወቀ፡፡

 

ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሠረት በቀለ ÷ኤጀንሲው ያስጸደቃቸው ደረጃዎች በምግብና እርሻ፣ በአካባቢና ጤና፣ በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች ፣ በኤሌክትሮ ኬሚካል እንዲሁም በኮንስትራክሽንና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች የተዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ደረጃዎቹ የፀደቁት በ33ኛውና በ34ኛው የብሔራዊ ምክርቤቱ ጉባኤ ላይ ሲሆን÷በስብሰባው ላይ በአምስት ዘርፎች ተዘጋጅተው የቀረቡት 400 ብሔራዊ ደረጃዎች መጽደቃቸውን ተጠቁሟል፡፡
ደረጃዎቹ ሲዘጋጁ አስፈላጊው ጥናትና ዳሰሳ የተደረገባቸው መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ÷ ለምክር ቤቱ ከቀረቡት 69 አዲስ ፣ 125 የተከለሱ እና 206 በማስቀጠል የፀደቁ ደረጃዎች መሆናቸውን አንስተዋል።
ዶክተር መሠረት አምራችና ሻጮች ደረጃዎቹ መኖራቸውን አውቀው አንዲጠቀሙ እና ደረጃዎቹንም ከተቋሙ ዶክመንቴሽን ክፍል መውሰድ እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡
በዓለምሰገድ አሳየ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.