Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻን በይፋ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደራስያን የዜጎችን አንድነት የሚያጠናክሩ ስራዎችን በማበርከት ለኢትዮጵያ ህልውና መጠበቅ የበኩላቸውን ሚና መውጣት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ገለጸ፡፡
የማህበሩ አባላት “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው እለት በተለያዩ ሁነቶች ያካሄደ ሲሆን፤ የማህበሩ አባላት የራሱን ህንጻ መገንባት በሚችልበት ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አበረ አዳሙ ደራስያን ኢትዮጵያ ካጋጠማት የህልውና አደጋ በድል እንድትሻገር በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ እንዲቆም ደራስያን ድርብ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም ነው ያነሱት።
ደራስያን የመከላከያ ሠራዊቱን ከመደገፍ በተጨማሪ ለሀገራቸው አንድነትና ህልውና መጠበቅ በሙያቸው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ተወካይ የሆኑት አቶ ዮናስ ምትኩ በበኩላቸው ማህበሩ አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራ ህብረ-ብሔራዊ ሀገር በመፍጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም ደራስያን በስራቸው እምቅ ባህላዊ ሃብቶቻችንን ማስተዋወቅ ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።
በተጨማሪ በስራዎቻቸው የህዝቡን አንድነት ማጠናከርና የአብሮነት እሴትን ማጽናት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው፤ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ህልውና ለመጠበቅ እያደረጉ ያሉትን ተጋድሎ ለመጪው ትውልድ የማስተላላፍ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በሌላ ዜና የማህበሩ አባላት “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል፡፡
የዘመቻው አስተባባሪ ኮሚቴ አባል አቶ ፋሲካው ሞላ ዘመቻው የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያውያን ዘመቻውን በመቀላቀል የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.