Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት ተመሰረተ።
ህብረቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ የዳያስፖራ ማህበራትን በማቀናጀት ለምስረታ መብቃቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገልጸዋል።
ማህበራቱ በየክልሎቻቸው የሚሰሩት ስራ እንዳለ ሆኖ የተለያዩ ማህብራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎችም አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በዳያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ችግር ከመፍታት ጀምሮ ሌሎችንም ከመንግስት እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመሆን በቅንጅት ለመስራትም እንደሆነ ተገልጿል።
በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሚፈጥሩት ህብረት ኢትዮጵያን በማስተዋወቅና በልማታዊ ስራዎች ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው ያሉት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ÷መንግስት ዳያስፖራውን በማህበር ማደራጀት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በቅጡ ይረዳል ብለዋል።
በመሆኑም በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የዳያስፖራ ማህበራት እንዲጠናከሩ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት ማህበራቱን በማስተባበር ለዳያስፖራው መብት መጠበቅ እንዲሁም አገሪቱ ጥቅም እንዲታገኝ ይስራል ብለዋል።
የማህበራቱ መጠናከር ማህበራሰቡን በተለያዩ መስኮች መጥቀም እንዲችሉ እድል ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑንም አምባሳደር ብርቱካን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት መመስረቱ ለማህበሩ አባላት መብት እና ጥቅም ከመስራት ባሻገር አጠቃላይ ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ እንዳለውም አብራርተዋል።
በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገር ውስጥ የተለያዩ የልማት መስኮች ተሰማርተው ለአገራቸውና ህዝባቸው አስተዋፇቸውን እንዲያጠናክሩም ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ህብረት መመስረቱ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በጋራ ተሳስረው መስራት እንዲችሉ ለማድረግ ታስቦ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.