Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ዻጉሜን 5 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን  የፕሪሚየር ሊግ ውድድር  በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው ፡፡

በመሆኑም  ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፣  ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት  ጨረታ እንደሚያወጣ ተነግሯል፡፡

ሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ  አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሂደት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው  ፡፡

የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.