Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊሸጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን በቴሌቪዥን ማስተላለፍ ለሚችሉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሀገራችን የሚካሄደው የወንዶች እግር ኳስ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ16 ክለቦች መካከል በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ በሚል የውድድር ፎርማት ይካሄዳል፡፡

በመሆኑም የሊጉ ኩባንያ በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የማስተላለፍ ፍቃድ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ ጨረታ ሊያወጣ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን ስም ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታ እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሊጉ ኩባንያ ከቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እና ከውድድር ስያሜ ሽያጭ የሚያገኘው ገቢ የኩባንያውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን የገንዘብ አቅም ያሳድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.