Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲጦዝ የፈለጉት የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው – አምባሳደር ዲና

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጠላቶች የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲጦዝ ቢፈልጉም ሁለቱ ሀገራቱ ጉዳዩን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት ቃል መግባታቸው ተገለጸ።

ችግሩን ለማስፋት የፈለጉት የኢትዮጵያ ጠላቶች እንዳልተሳካላቸው እና እንደማይሳካላቸው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሱዳን በኩል ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር አንስተው፤ ጥቃቱም በታችኛው መዋቅር የተፈጸመ መሆኑንም ነው የገለጹት።

ችግሩ ከሱዳን መንግስት ጋር የተያያዘ አይደለም ያሉት አምባሳደር ዲና ጉዳዩን ለማጦዝና ክፍተት ለመፍጠር ሴራ ሲሸርቡ የነበሩ አካላት ግን እንደነበሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ጠቅሰዋል።

አጋጣሚውን በማስፋት ችግር ለመፍጠር የተሯሯጡት ሁሉ አልተሳካላቸውም፥ ወደፊትም ቢሆን አይሳካላቸውም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ጠላቶች ጉዳዩን ለማጦዝ ቢዳክሩም የድንበር ጥያቄው በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል ብለዋል ቃል አቀባዩ።

በጂቡቲ በተካሄደው 38ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የመሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በጉዳዩ ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

በውይይቱም ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳዩን ለመፍታት ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።

በብስራት መለሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.