Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ቱርክ የፖለቲካ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)6ኛው የኢትዮ ቱርክ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ዛሬ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ ልኡክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ ሰሆን፤ የቱርክ ልኡክ በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሴዳት ኦናል አማካኝነት ተመርቷል።

በምክክር መድረኩ ላይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እና ቱርክ ረጅም ዘመናትንያስቆጠር ግኙነት እንዳላቸው በማስታውስ፤ የቱርክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ከቀዳሚ አገራት ተርታ እንደሚሰለፉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ቱርክ ካላቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር በተጨማሪ በትምህርት፣ በጸጥታ እና ሽብርን በመከለካል በትብብር ሊሰሩ የሚችሉባቸው ዘርፎች እንደሆኑም አምባሳደር ሬደዋን ገልጸዋል።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሴዳት ኦናል በበከላቸው ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ላለት ግንኙነት ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ በመግለጽ ፤ ትብብሯን ለማጠናከር ትስራለች ብለዋል።

በሁለቱ አገሮቸ መካከል የሚደረጉ መሰል የፖለቲካ ውይይቶች ተጠናከረው መቀጠል እንዳለባቸውም አምባሳደር ሴዳት በንግግራቸው አንስተው በኢትዮጵያ መዋለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ የቱርክ ባለሃበቶችን ለመደገፍ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታ ሴዳት ገልጸዋል።

ሁለቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተም መረጃ የተለዋወጡ ሲሆን፤ የበሽታውን ስርጭት ለመግታትም ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.