Fana: At a Speed of Life!

“የኢትዮ-ፓኪስታን ሳይንትፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም” ሊመሰረት ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)”የኢትዮ-ፓኪስታን ሳይንትፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም” ሊመሰረት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ፎረሙ በሳይንቲፊክ ጉዳዮች ዙሪያ ኢትዮጵያና ፓኪስታን ያላቸውን ልምድ እንዲለዋወጡና በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ ከፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ ጋር የኢትዮ-ፓኪስታን ሳይንትፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም ምስረታና ሁለቱ ሀገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በውይይቱ ዶክተር በለጠ ፎረሙ እንዲመሰረት ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶችን በማጠናከር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

ፎረሙ በሀገራቱ መካከል የሳይንስና ቴክኖሎጂ የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ይረዳል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ለፎረሙ ስኬት ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ትወጣለች ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሾዛብ አባስ በበኩላቸው ÷የሳይንትፊክ ፎረሙ በአይቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውሃ ቴክኖሎጂ፣ በጤና እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ምርምር የሚያደርግና የዕውቀት ሽግግር የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ፓኪስታን “የኢትዮ-ፓኪስታን ሳይንትፊክ ዲፕሎማሲ ፎረም” እንዲመሰረት ጥያቄ ባቀረበችው መሰረት ነው ከስምምነት የተደረሰው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.