Fana: At a Speed of Life!

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን በወሎ ግንባር በመገኘት የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን በወሎ ግንባር በመገኘት የ1 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስና አይነት ድጋፍ ለሰራዊቱ አድርጓል።
ኮሚሽኑን በመወከል ድጋፍ ያደረጉት ኮሚሽነሯ ወይዘሮ ለሊሴ ነሜ እንደተናገሩት ድጋፉ ከሰራተኛው የተሰበሰበ ሲሆን በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
የመከላከያ ሰራዊቱ በሚያደርገው ተጋድሎ ሁልጊዜም ኮሚሽኑና ሰራተኛው ለወደፊትም ከጎኑ በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
መከላከያን በመወከል ድጋፉን የተረከቡት ሌለታን ኮሎኔል ሌቺሳ መገርሳ እንደተናገሩት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ የጣለባቸዉን አደራ ከዳር ለማድረስ ሰራዊቱ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።
በብስራት መንግስቱ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.