Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና አሪፍፔይ በዲጂታል ክፍያ ስርአት ላይ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) እና አሪፍፔይ የዲጂታል ክፍያ ስርአት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት በኢመደኤ የደራሽ የዲጂታል ክፍያ ፕላትፎርም ዳይሬክተር ብሩክ ወልደየስ÷ ኤጀንሲዉ ህብረተሰቡን ይጠቅማሉ ባላቸዉ ጉዳዮች ከመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተበበር እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ ከአሪፍፔይ ጋር የተደረሰዉ ስምምነት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
የአሪፍፔይ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃብታሙ ታደሰ በበኩላቸዉ፥ ኩባንያቸው ከደራሽ ፕላትፎርም ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸዉ ከዘጠና ከመቶ በላይ ግብይት እየተደረገበት ያለዉን የጥሬ ገንዘብ ልዉዉጥ ጥገኝነትን ይቀንሳል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች ከተለያዩ ተቋማት ላገኙት አገልግሎት ክፍያዎችን በተቀላጠፈና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በቀላሉ ለመክፈል ያስችላቸዋልም ብለዋል፡፡
አሪፍፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂ መሆኑን እና አንድ ተጠቃሚ አካዉንቱን ከአሪፍፔይ መተግበሪያ ጋር ሊንክ በማድረግ ባለበት ቦታ ሆኖ የውኃ፣ መብራት፣ የትምህርት፣ የታክሲ፣ የሱፐር ማርኬትና ሌሎች የግብይት አገልግሎቶችን ለመፈጸም ያስችላል ብለዋል።
ደራሽ የዲጂታል ክፍያ ፕላትፎርም ከ16 ባንኮች ከ10 ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል መባሉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.