Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን  ስምምነት  በዛሬዉ እለት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የኮርፖሬሽኑን መሰረተ-ልማት ወደ ዲጂታል ስርአት እንዲገባ የማድረግ እና የሳይበር ልማት ስትራቴጂክ ማፕ የማዘጋጀት እንዲሁም የመረጃዎቹን ደህንነት ማስጠበቅን የካተተ እንደሆነ ታዉቋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በስምምነቱ ወቅት÷  መሬት ዋነኛ ሀብት በመሆኑ የዚህን ሀብት መረጃ በተገቢው መንገድ መጠቀም እና ማስቀመጥ ለሀገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ሹመቴ አክለውም መረጃ አሁን ባለንበት ዘመን ትልቁ እና ቁልፍ መወዳደሪያ እንደሆነ ጠቁመዉ÷ ይህንን መረጃ ደህነነቱን ለማስጠበቅ እና ለመጠቀም የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በሚያከናውናቸው ስራዎች ላይ ኤጀንሲው በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በበኩላቸዉ ÷ትልቅ ሀብት የሆነው የመሬት ነክ መረጃ መያዝ ሀገራችን በምትከውናቸው የመሰረተ- ልማት ስራዎች ላይ ጥራት ያለው ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለውም ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር የተደረገው ስምምነት የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽኑ በቴክኖሎጂ ራሱን ለማዘመን በሚከውናቸው ሰራዎች ላይ ማእከል ያደረገ  ሲሆን በተለይ መረጃን ደህንነቱን ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ መግለጻቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.