Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሐብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ ከህዋዌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶች ለማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስቴር መሥሪየ ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን መሠረተ ልማቱን ማዘመንና የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብና አሠራሩን ለማቀላጠፍ ፍላጎት እንዳለው ነው ሚኒስትሩ በውይይቱ የተናገሩት፡፡

ህዋዌ ኢትዮጵያም የበኩሉን ምክረ ሀሳብ በማቅረብ ትብብር እንዲያደርግ ሚኒስትሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የህዋዌ ኢትዮጵያ አመራሮች በበኩላቸው ÷የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቱን በምን መልኩ ቢያዘምን ውጤታማ እንደሚሆን በሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት የሠሩትን ሥራ መሠረት በማድረግ ሀሳብ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.