Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የመደገፍ ተልዕኮውን እንዲወጣ እየተሰራ ነው – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የመደገፍ ተልዕኮውን እንዲወጣ አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ የዘርፉን የ2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የ2015 በጀት ዓመት አቅድን በሚመለከት ከክልሎች የዘርፉ ቢሮ ኃላፊዎችና ከተጠሪ ተቋማት አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ መድረኩ ሀገራዊ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎችና ተግዳሮቶች ላይ ብትሆንም መንግስትና ክልሎች በመተሳሰብና በመቀራረብ ከሰሩ ችግሮችን መሻገር ይቻላል ብለዋል።

ችግሮችን መሻገር የሚቻለው እውቀት መር የአሰራር ስርዓት ሲሰፍን መሆኑን ጠቅሰው÷ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ደግሞ እውቀት መር የችግሮች መፍትሔ ለማምጣት ያግዛልም ነው ያሉት።

በ2014 በጀት ዓመት ለክልሎች አቅም የሚሆኑ የፖሊሲ፣ የሕግ ማዕቀፍና እና ለ2015 እቅድ መነሻ የሚሆኑ ስራዎች እንደተከናወኑም ነው የገለጹትተ።

የሌሎች ሀገራት የትናንት የእድገት ምንጭ የተፈጥሮ ሃብት ወይም ሌላ ሊሆን እንደሚችል ገልጸው÷ የዛሬው ዘመን የእድገት ሚስጥር የሚቀዳው ግን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ መሆኑ ተረጋግጦ ያደረ ሐቅ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ።

እንደ ኢትዮጵያ የተቀመጠው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆንና ዘርፉ የሚጠበቅበትን የኢኮኖሚ አመንጭነትና የአስቻይነት ጣምራ ሚናውን እንዲወጣ በሁሉም ክልሎች መንግስታት ዘንድ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በዘርፉ እንደ ሀገር የተሰጠው ትኩረት በሁሉም ክልሎች ስላልተሰጠ ሁሉም አካላት ትኩረት እንዲሰጡበት አስፈላጊውን ድጋፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚያደርግ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.